
ቢሮው የ6 ወራት አፈፃፀሙን ከባለድርሻ አካላት እና ከሙያ ማሕበራት ጋር ገመገመ፡፡
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙን አብረውት ከሚሰሩት ስራ ተቋራጮች ፣ አማካሪዎች ፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም ተሳስሮ ከሚሰራቸው የሙያ ማሕበራት ጋር በመሆን ገምግሟል፡፡
በመድረኩ ቢሮው አሁን እያሳየ የሚገኘው ወቅታዊ የአፈፃፀም ከፍታ እንዲሁም በተለይ ኢንተርፕራይዞችን ለማብቃት ብሎም ተወዳዳሪ ለማድረግ እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራት በተሳታፊዎች ዘንድ ዕውቅና የተቸረው ሲሆን ተያይዞም ከሙያ ማሕበራት ጋር የነበረው የ6 ወራት አፈፃፀም ተገምግሞ በተከለሰ ዕቅድ ላይ የስምምነት መፈራረም ተችሏል፡፡
በዚህ መድረክ ከኢትዮጵያ ስራ ተቋራጮች ማሕበር ፣ ከኢትዮጵያ አማካሪዎች ማሕበር እንዲሁም ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ማሕበር የተወከሉ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጥር 21/2017 ዓ/ም
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments